ደም መለገስ በፍላጎት/በፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ የሚደረግ በጎ ተግባር ነዉ፡፡ እርስዎ ደም ለመስጠት ተስማምተሁ ከለገሱ በኃላ ደሙ ለሌላ የሰዉ ደም ለሚያስፈልገዉ ግለሰብ ይለገሳል፡፡

በየአመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሌላ ሰዉ ደም ይፈልጋሉ፡፡ አንዳንዶቹ በቀዶ ጥገና ጊዜ የሚፈልጉ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ከአደጋ በኃላ ወይም የዉስጥ ደዌ ችግር ኖሮዋቸዉ ደም ወይም የተወሰኑ የደም ሴሎችን በሚፈልጉበት ወቅት ነዉ፡፡ ስለሆነም ደም መለገስ እነዚህንና ሌሎችንም ችግሮች ይፈታል፡፡

የደም መለገስ የሚመጣዉ ችግር አለ?
ደም መለገስ የሚያመጣዉ ምንም ችግር የለም!!!

ለያንዳንዱ ለጋሽ አዲስና ጤንነቱ የተጠበቀ ዕቃዎች ስለሚጠቀሙ ደም በመለገስዎ በደምና በደም ንኪኪ ሊተላለፉ የሚችሉ ኢንፌክሽኖች ሊይዝዎ አይችሉም፡፡
እርስዎ ጤናማ ከሆኑ ጤንነትዎ ላይ ምንም አይነት አደጋ/ችግር ሳይከተል ደም መለገስ ይችላሉ፡፡ ደም በለገሱ በ24 ሰዓታት ዉስጥ ሰዉነትዎ ደም በመለገስ ወቅት ያጣዉን የፈሳሽ መጠን የሚተካ ሲሆን በተወሰኑ ሳምንታት ዉስጥ ደግሞ ሰዉነትዎ በደም መለገስ ወቅት ያጣዉን ቀይ የደም ሴሎችን ሙሉ በሙሉ ይተካል፡፡

ደም ለመለገስ የሚደረጉ ዝግጅቶች

ሙሉ ደምም ይሁን ፕላዝማና ፕላትሌትስ ከመለገስዎ በፊት ሊሟሉ የሚገባቸዉ ነገሮች፡-

 • ሙሉ ጤነኛ መሆን
 • ቢያንስ 18 አመትና ከዚያን በላይ መሆን፡-ደም ለመለገስ መነሻ ዕድሜ ከሀገር ሀገር የሚለያይ ሲሆን የላይኛዉ እድሜ ጣሪያ ግን ገደብ የለዉም፡፡
 • ክብደትዎ ቢያንስ 45 ኪሎግራም መሆን፡፡
 • አካላዊና ሌሎች የጤና ምርመራ ማለፍ የሚችል መሆን አለበት፡፡

የሰዉነት ቀጭንና ወፍራም መሆን ደም ለመስጠት/ለመለገስም ሆነ ላለመለገስ እንደ ቅድመ ሁኔታ አያገለግልም፡፡ ይልቁንም ከላይ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያሟሉ ከሆነ ሰዉነትዎ ቀጭን ቢሆኑም እንኳ መለገስ ይችላሉ፡፡

ደም ለመለገስ ካሰቡበት ቀን በፊት ባለዉ ምሽት በቂ እንቅልፍ ማግኘት የሚያስፈልግ ሲሆን ከመለገስዎ በፊት ጥናማ ምግብ መመገብ፤ ስብነት ያለቸዉን( ለምሳሌ የአሳማ ስጋ)ና እንደ አይስ ክሬም ያሉ ምግቦችን ያለመመገብ፤ እስከ 473 ሚሊ ሊትር የሚደርስ ተጨማሪ ፈሳሽ ከመለገስዎ በፊት መጠጣት መቻልና ፕላትሌትስ የሚለግሱ ከሆነ ከመለገስዎ ከሁለት ቀናት በፊት ጀምሮ አስፒሪን ያለመዉሰድ ይመከራሉ፡፡

የሚከተሉት ሰዎች ደም ለመለገስ ብቁ አይደሉም:-

 • ያለ ሀኪም ትዕዛዝ በመርፌ የሚወጉ እንደ ስቴሮይድና ህገወጥ መድሃኒቶችን የሚጠቀሙ/የተጠቀሙ ሰዎች
 • ከዚህ በፊት ክሎቲይንግ ፋክተርስ መድሃኒቶችን የተጠቀሙ/ወስደዉ የሚዉቁ ሰዎች
 • የኤች አይቪ ቫይረስ በደማቸዉ ያለባቸዉ ሰዎች
 • የግብረስጋ ግንኙነትን ለገንዘብ ወይም ለህገወጥ መድሃኒቶች ማግኛ የሚጠቀሙ ግለሰቦች
 • በደማቸዉ የሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ ያለባቸዉ ሰዎች

የተወሰኑ አካለዊ ምርመራዎች(የደም ግፊትዎን መለካት፣ የሰዉነት ሙቀትዎንና የልብ ትርታዎ) ቼክ ሊደረግልዎ ይችላል፡፡ ትንሽ ደም ተወስዶ የቀይ የደም ሴልዎ መጠን ይታያል፡፡ ቀይ የደም ሴል መጠንዎ ችግር ከሌለበትና በሌሎች ምርመራዎችም ብቁ ከሆኑ ደም መለገስ ይችላሉ፡፡
ደም ከለገሱ በኃላ ለተወሰነ ጊዜ መቆያ ክፍል ዉስጥ እንዲያርፉ ተደርገዉ ቀለል ያሉ መክሰሶችንና የሚጠጡ ነገሮችን እንዲያገኙ ይደረጋሉ፡፡ ከዚያን ከ 15 ደቂቃዎች በኃላ ወደ ጉዳዮ እንዲሄዱ ይደረጋሉ፡፡

ደም ከለገሱ በኃላ፡-

 • ተጨማሪ ፈሳሽ ለቀጣይ አንድ ወይም ሁለት ቀናት መዉሰድ
 • ለአምስት ተከታታይ ቀናት ከባድ ስራ ያለመስራት/ከባድ ዕቃ ያለማንሳት
 • የራስ ምታት/የማዞር ስሜት ከተሰማዎ ስሜቱ እስኪያልፍልዎ ለተወሰነ ጊዜ እግርዎን ወደላይ አድርገሁ ይንጋለሉ፡፡
 • ደም ለመለገስ የተወጉበት ቦታ ላይ የታሰረልዎን ባንዴጅ/ፕላስተር ቢያንስ ከ4-5 ሰዓታት ያለመፍታት
 • ባንዴጁን/ፕላስተሩን ከፈቱ በኃላ ቢደማብዎ ቦታዉ ላይ ጫን አድርገዉ በመያዝና እጅዎን ከፍ አድርገዉ በመያዝ ለአምስት ደቂቃዎች መቆየት
 • መርፌ የተወጉበት ቦታ ላይ ባለዉ ቆዳዎ ስር ደም መፍሰስ ወይም መቅላት ካለዎ በረዶ አልፍ አለፍ እያሉ ለመጀመሪያ 24 ሰዓታት መያዝ
 • እጅዎን ካመመዎ እንደ አሴታሚኖፌን/ፓራስታሞል ያሉ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን መዉሰድ፡፡ ነገር ግን እንደ አስፒሪን ወይም አይቡፕሮፌን(አድቪል) የመሳሰሉ መድሃኒቶችን ከመዉሰድ ይቆጠቡ፡፡

 

Pin It