ታክሲዎች ከመደበኛ የመጫን አቅማቸው በግማሽ ቀንሰው እንዲጭኑ ውሳኔ ተላልፏል

ታክሲዎች ከመደበኛ የመጫን አቅማቸው በግማሽ ቀንሰው እንዲጭኑ ውሳኔ ተላልፏል።

12 ሰው የመጫን አቅም ያለው ሚኒባስ ታክሲ 6 ሰው ብቻ እንዲጭኑ ተደርጓል፡፡

ሌሎች ተጨማሪ ወንበር ያላቸው እንደ ዶልፊን ታክሲዎች እንደወንበራቸው አቅም በግማሽ ቀንሰው ይጭናሉ፡፡

በሃይገር ባስ የተሳፋሪ ቁጥር በወንበር ልኩ በግማሽ ብቻ እንዲጭኑ የተደረገ ሲሆን፥ 14 ሰው ብቻ እንዲጭኑ ውሳኔ ተላልፏል፡፡

አንበሳ የከተማ አውቶቡስ እና ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አውቶቡሶች 40 ሰው ይጭን የነበረ መደበኛ አውቶቡስ 30 ሰው ብቻ የሚጭኑ ይሆናል፡፡

ረጃጅሞቹ የተማሪ አውቶቡሶች 30 ሰው ብቻ እና አጫጭሮቹ የተማሪ አውቶቡሶች 20 ሰው ብቻ እንዲጭኑ፤ እንዲሁም ደብል ዴከር አውቶቡሶች 50 ሰው ብቻ እንዲጭን ተወስኗል፡፡

ታክሲዎችና ሃይገር አውቶቡሶች የመጫን አቅማቸው ወደ መደበኛው እስኪመለስ ቀደም ሲል የነበረው ታሪፍ በእጥፍ አድጎ ተሳፋሪዎች እንዲከፍሉ ተደርጓል ፡፡

የአንበሳ እና የሸገር አውቶቡሶች ታሪፍ በነበረበት የሚቀጥል ሆኖ መንግስት በሚያደርገው ድጎማ እንዲሸፈን ይደረጋል፡፡

ማንኛውም ከተፈቀደው ሰው በላይ ጭኖ ውጭ ሲሰራ የተገኘ ታክሲም ሆነ የሃይገር አውቶቡስ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ይቀጣል።

በተጨማሪም የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃድ እስከመጨረሻው እንዲታገድ በማድረግ በሌሎች የሀገሪቱ ህጎች ተጠያቂ የሚደረጉም ይሆናል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክረተሪያት