የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለጤና ባለሙያዎች መስጠት ለጤናው ሴክተር የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ለጤና ባለሙያዎች ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ሙያዊ ችሎታቸውን የሚያድግበትን የአቅም ግንባታዎችን

ማመቻቸት ለሀገራችን የጤናው ሴክተር የሚሰጠው ጠቀሜታ እጅግ የላቀ እንደሆነ ተገለጸ፡፡ የኢትዬዽያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ የኤካ ኮተቤን አጠቃላይ ሆስፒታል የስልጠና ማዕከል መርቀው በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር እንዳስታወቁት ወቅቱና የዘመኑ ሳይንሱ የሚጠይቀውን ልዩ ልዩ ሙያዊ የአቅም ማጎልበቻ  ስልጠናዎችን ለጤና ባለሙያዎች በመስጠት ሙያዊ ክህሎታቸውን ማጎልበት መቻል ለጤናው ሴክተር የዕለት ተዕለት ስራ ውጤታማነት የሚሰጠው እገዛ ከፍተƒ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ አቶ አስቻለው አባይነህ  አያይዘውም ሀገራችን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል ረገድ በምታደርገው ጥረት ያልተቆጠበ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩትን አካላት በሙሉ አመስግነው በተለይ ለስልጠና ማዕከሉ ልዩ ልዩ ድጋፍ ላደረጉት ለኮርያ መንግስት እና የአለም ጤና ድርጅት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የኮርያ መንግስት ተወካይ እና በኢትዬዽያ የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶ/ር ቦሩማ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በቀጣይም የሚያደርጉትን ትብብርና ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡