የፀሀይ መከላከያ/sunscreen ማለት ስንቀባው ፊታችንን ከፀሀይ ብርሀን የሚከላከልልን ቅባት ሲሆን ያለሀኪም ትዕዛዝ ልንገዛው እንችላለን።

~ ጉዳት የለውም
~ ማንኛውም ሰው ቢቀባው ከቆዳ ማርጀት፣ መጥቆር ፣ ከቆዳ ካንሰር ራሱን ይጠብቃል።
.
~ የመከላከል ብቃታቸው/spf/ ~ባለ 15፣30፣45፣60 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ቁጥሩ በጨመረ ቁጥር የመከላከል ብቃታቸው እየጨመረ ይሄዳል።
፦15 spf ያለውን መቀባት ብዙም ውጤታማ አይደለም።
.
~ የሚሰሩበት ፎርም በ ጄል ፣ ሎሽን፣ ክሬም፣ ኦይንትመንት መልክ ነው።
 ፦ወዛማ ቆዳ ላይ ጄልና ሎሽን አልፎ አልፎም ባለ ክሬም መከላከያዎች ተመራጭ ናቸው።
፦ደረቅ ላለ ፊት ኦይንትመንትና ክሬም ተመራጭ ናቸው።
.
~ በየቀኑ ከቤት ውስጥም ቢሆኑ መቀባት አይዘንጉ።
~ ጥዋትና ምሳ ሰአት ይቀቡ።
.
ዶ/ር ስምረት መስፍን : የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት

 

Pin It