በቁጥጥር ስር ያልዋለ የስኳር ህመም ሊያመጣቸው የሚችላቸው የጤና ችግሮች

በቁጥጥር ሥር ያልዋለ የስኳር ሕመም መዘዙ ብዙ ነው። የሐኪም ምክር መስማትና ክትትል ማድረግ ችግሩን ይቀንሰዋል። እስቲ ሕመሙ የሚያመጣውን የጤና ችግር እንመልከት።

የኩላሊት ጉዳት ፡- ኩላሊት ቆሻሻን የሚያጣራበት ክፍል በመጉዳት ኩላሊት ስራ እንዲስተጓጎልና ብሎም አንዲቆም ያደርጋል፡፡

የነርቭ ጉዳት ፡-ለነርቭ ምግብ የሚያቀብሉትን ጥቃቅን የደም ስሮችን በመጉዳት የነርቮች ስራ መስተጓጎል ያመጣል። በተለይ በእግር እና በእግር ጣቶች ጫፎች ላይ የሚገኙት ነርቮች እንዲጎዱ በማድረግ የእግር ጉዳት ቁስል እና ጉዳቱ ሲብስ ደግሞም ለእግር መቆረጥ ሊዳርግ ይችላል፡፡

የዓይን ጉዳት ፡- ለዓይናችን ምግብ የሚያቀብሉትን ጥቃቅን የደም ስሮችን በመጉዳት ዓይናችንን ብርሃኑን እንዲያጣ ሊያደርግ ይችላል፡፡ሞራ ለመሳሰሉ የዓይን እክሎች ሊያጋጥም ይችላል፡፡

የልብ ሕመም ፡-በቁጥጥር ስር ያልዋለ የስኳር ህመም የልብ እና ተያያዥ ችግሮችን በተለይም የልብ ድንገተኛ እና በሂደት የሚመጣ ድካም እና ከፍተኛ የደም ግፊት ለመሳሰሉ ችግሮች በከፍተኛ ሁኔታ ያጋልጣል፡፡

የደም ቧንቧዎች መጥበብ ፡-የደም ቧንቧዎች ቁጥጥር ስር ባልዋለ የስኳር መጠን የሚመጡ ችግሮች ምክንያት ይጠባል፡፡በዚህም የተነሳ ደም እንደልብ በሰወነታችን ለመዘዋወር አይችልም ፡፡

ስትሮክ፡-በጭንቅላታችን ውስጥ ያለው የደም ቧንቧ ቁጥጥር ስር ባልዋለ ስኳር የተነሳ በሚከሰቱ ችግሮች እጅግ ጠቦ በሚዘጋበት ወይም በሚጎዳበት ጊዜ ለጭንቅላታችን ህዋሳት የሚደርሰው ኦክስጂን እያነሰ ይሄድ እና ስትሮክ ተብሎ ለሚመጣው የጤና ችግር የመጋለጥ አጋጣሚዎችን ይጨምራል፡፡ይኸውም በደም መፍሰስ ወይም መርጋት የሚመጣ ችግር ነው፡፡