የጡት ካንሰር ቅድመ ልየታ (breast cancer screening )

የጡት ካንሰር ቅድመ ልየታ በማሞግራፊ (mammography ) እና አካላዊ የጡት ምርመራ ናቸው ።

ከአንድ በላይ የጡት ካንሰር በቤተሰብ ውስጥ ካለ ታሞክሲፊን (tamoxifen) ያለውን ሪስክ በግማሽ ይቀንሳል ።
ከ10 ሰዎች 1 የጡት ካንሰር ተጠቂዎች ከ45 ዓመት በታች ያሉ ናቸው ።

የጡት ካንሰር ቅድመ ልየታ በእድሜ መሰረት
? ከ20-39 ዓመት ላሉ ሴቶች
1. በራስ የሚደረግ ወርሃዊ የጡት ምርመራ ( monthly self bresat examination )
2. በህክምና ባለሙያዎች የሚደረግ አካላዊ የጡት ምርመራ ( clinical breast examination ) በየ 3 ዓመቱ
? ከ40-49 ዓመት
1. በራስ የሚደረግ ወርሃዊ የጡት ምርመራ ( monthly self bresat examination )
2. በህክምና ባለሙያዎች የሚደረግ አካላዊ የጡት ምርመራ ( clinical breast examination ) በየዓመቱ
3. የመጀመሪያ ማሞግራፊ (mammography ) 40 ዓመት ላይ ጀምሮ በየ 2 ዓመቱ ማድረግ
? ከ50 ዓመት በላይ
1. በራስ የሚደረግ ወርሃዊ የጡት ምርመራ ( monthly self bresat examination )
2. በህክምና ባለሙያዎች የሚደረግ አካላዊ የጡት ምርመራ ( clinical breast examination ) በየዓመቱ
3. ማሞግራፊ (mammography ) በየአመቱ ማሰራት ይመከራል ።