ልጄ 6ወር ሞልቶታል ምን ልመግበው?

ህፃናት የተስተካከለ አካላዊና አዕምሮዊ እድገት እንዲኖራቸው ጤናማና የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት ይኖርባቸዋል ።

ከ6ወር ጀምሮ ያሉ ህፃናት የእናት ጡት ወተት ለብቻው የምግብ ፍላጎታቸውን ስለማያሟላ ተጨማሪ ሌሎች ምግቦችን መጀመር ይኖርባቸዋል ::

?ተጨማሪ ምግብ  (supplementary food) ፡- ማለት እድሜያቸው ከ6ወር በላይ የሆናቸው ህፃናት ቀድሞ ይወስዱት የነበሩት የእናት ጡት ወይም የጣሳ ወተት በዋናነት እንዳለ ሆኖ በእርሱ ላይ የሚጨመር ምግብ ማለት ነው።

?ለምን በ6ወር? ከዛበፊት ወይም በኃላ ቢጀመርላቸውስ??

ከ6ወር በፊት የህፃናት አንጀት ከምግብ ጋር ተቀላቅሎ ሊመገቡት የሚችሉትን የተለያዩ ባክቴሪያዎች የመቋቋም አቅም ስለሌለው  በቀላሉ ለተቅማጥና ለቱከት በሽታ ስለሚጋለጡ ተጨማሪ ምግብ መጀመር የለበትም ።

ከ6 ወር በኃላ ዘግይቶ መጀመር  ህፃኑ በቂ የሆነ ክብደ ት እንዳይጨምር እና የተለያዩ ንጥረ ነገሮች  እና ቫይታሚን እ ጥረት እንዲያጋጥመው ያረጋል ::

?ምን ልንመግባቸው እንችላለን?

1-የእህል ዘሮች ፡- አጃ፥ስንዴ፥ገብስ፥ሩዝ፥በቆሎ ፥ጤፍ

2- ጥራጥሬ-  አተር፥ ባቄላ ፥ሽንብራ

3-አትክልት-የተፈጨ ካሮት፥ድንች፥ስኳር ድንች፥ጎመን፥ፎሶሊያ፥ዝኩኒ ???

3-ፍራፍሬ-የተፈጨ  አቮካዶ፥ሙዝ፥አፕል፥ፓፓያ፥ማንጎ????

4- የእንስሳት ተዋዕፃ - የዶሮ ስጋና የበሬ ስጋ መረቅ(ሾርባ)

5-ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች  ለምሳሌ

?ብረት(iron) - ይህም ቀይ ደም ሴልን ለመስራት የሚያገለግል ሲሆን በአብዛኛው ከጥራጥሬዎችና ከእህል ዘሮች የሚገኝ ሲሆን፤የተመጣጠነ ምግብ የማይመገቡና የላም ወተት ከአንድ አመት በታች የሚጠጡ ህፃናት በብረት ማነስ አማካይነት የሚመጣ ደም ማነስ( iron deficiency anemia)  ሊይዛቸው ይችላል፤ይህ ሲከሰት የህፃናት ሐኪም በማማከር ያስፈልጋል

?-ካልሲየም (calcium)- ለአጥንትና ለጥርስ ፤ በአጠቃላይ ለነርቭና ለሴሎች እንቅስቃሴ የሚጠቅም ንጥረ ነገር ሲሆን ከእናት ጡት ወተት፤ ካልሽየም ካላቸው የጣሳ ወተቶችና ከአትክልቶች ይገኛል

?-ቫይታሚን ዲ (vitamin D)- ቫይታሚን ዲ በምግባችን ውስጥ ያለውን ካልሼም (calcium) ሰውነታችን እንዲጠቀምበት በማድረግ ጤናማ የአጥንት እድገት እንዲኖር ይረዳል የጥዋት ፀሐይ 3-4ሰዓት 15- 30ደቂቃ ቅባት ሳይቀቡ ማሞቅ ያስፈልጋል፤ አብዛኛውን ጊዜ ህፃናት ቤት ውስጥ ስለሚውሉ አድገው ደጅ ላይ መጫወት እስከሚችሉበት ጊዜ ድረስ መቀጠል አለብን

?ውሃ (water) - የእናት ጡት ወተት በቂ ውሃ ስላለው ከስድስት ወር በፊት ተጨማሪ ውሃ አያስፈልገውም። አሁን ግን ተጨማሪ ምግብ ሲጀምሩ ፈልቶ የቀዘቀዘ ንጹህ ውሃ በቀን 100-200ሚ.ሊ. እዲወስዱ  ይመከራል

??የምጥን ዱቄት በሃገራችን አብዛኛው እናቶች በገንፎና በአጥሚት መልክ ለልጆቻቸው የሚመግቡት ሲሆን  ይሄም በውስጡ የተለያዩ ከእህል ዘሮችን አካቶ የሚዘጋጅ ነው ለምሳሌ
ሦስት እጅ ከእህል ዘሮች ማለትም የተፈተገ ስንዴ፥ ጤፍ፥ አጃ፥ተፈትጎ የተቆላ ገብስ  እና የመሳሰሉት
አንድ እጅ ከጥራጥሬ አይነቶች   ሽንብራ፥ አተር፥ባቄላን  አካቶ የሚዘጋጅ ነው።

? ገንፎ (porridge) በሁሉም ኢትዮጵያዊ ቤት በቀላሉ ሊገኝ የሚችል በውስጡም ብዙ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ስለሆነ ልጆች እንዲወዱት ለስለስ ተደርጎ ተዘጋጅቶ እንዲሰጣቸው ይመከራል

??እንዴት እንመግባቸው?

-?የህፃናት የመጀመሪያ ምግብ ከፊል ፈሳሽ መሆን አለበት፤ያልተፈጨ ምግብ መሰጠት የለበትም ትንታን ያስከትላል  
-?በቀን አንድ አይነት ምግብ አንድ ጊዜ ብቻ ለሶስት ተከታታይ ቀናት መስጠትና  የአለርጂ ምልክት ለምሳሌ ሽፍታ ፥ቱከት፥ተቅማጥና የመሳሰሉትን  ካሳዩ ምግቡን ወዲያው ማቆም
- ?በሁለት ወይም በሦስት አይነት ምግብ በቀን መጀመር አይመከርም ፤ ምክንያቱም ድንገት አለርጂ ቢፈጠር ከየትኛው ዓይነት ምግብ እንደሆነ ለመለየት ያስቸግራል
-?በትንሹ መጀመር፤ ለመጀመሪያ ከሦስት እስከ አምስት ማንኪያ ከበሉ ይበቃል፤ እንደ ህፃኑ አቀባበል በየቀኑ መጠኑን እየጨመሩ መሄድ ያስፋልጋል
-?ምግቦችን በየሦስት ቀን እየቀየርን በመስጠት የተለያዩ ምግቦችን ከለመዱልን በኃላ፤ የተስማማቸውን ምግብ በየ 3 ሰዓት ልዩነት እየቀያየርን  መመገብ
-?ህፃናት ታመው እያለ አዲስ ምግብ መጀመር አይመከርም፤ አለርጂን ከበሽታው ለመለየት ስለሚያስቸግር
ዶ/ር ትዕግስት አርጋው የህፃናት ህክምና እስፔሻሊስት