የአፍንጫ አለርጂ

የአፍንጫ አለርጂ

የአፍንጫ አለርጂ እንደ አስም ሁሉ ትክክለኛ መንስሔው ባይታወቅም ህመሙን በሚቀሰቅሱት ወይም በሚያባብሱት ሁኔታዎች እንዲሁም በህመሙ አጠቃላይ ባሕሪና ዕድገት ተመሳሳይነት አላቸው፡፡

ህመሙ የሚገለፀው በማስነጠስ፣ውሃ የመሰለ የአፍንጫ ፈሳሽ፣አፍንጫን ማፈን ዓይንና ጉሮሮን ማሳከክ ፣ዕምባ መፍሰስ ፣ራስ ምታት በድንገት በመቀስቀሱናሲያሰኘው ደግሞ ያለምንም መድኃኒት ለጊዜው በመልቀቁ ነው፡፡

ብዙን ጊዜ ህመሙ የሚቀሰቀሰው በአበባ ብናኝ፣ ፣የውሻና የድመት ዕዳሪ፣ ሽቶ፣አቧራ፣ኬሚካል፣የሰው ጠረን፣የጫማ ሽታና እንዲሁም በቅዝቃዜ በሽንት ቤትና በከብቶች በረት ነው፡፡

የሚከተሉትን ጠቃሚ ምክሮች ማድረግ ከችግሩ ለመውጣት ይረዳል
• የታዘዘን መድኃኒት በአግባቡ መውሰድ
• ውሃ አፍልቶ ባዶውን መታጠን
• ውሃና ጨው አፍልቶ በአፍንጫ መሳብ
•  የሚቀሰቀሱ ወይም የሚያባብሱ ነገሮችን ማስወገድ
• ከተቻለ የሥራና የመኖሪያ አካባቢን መቀየር
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በየቀኑ መሥራት
• በብርድ ጊዜ አፍንጫን መወተፍ ወይም መሸፈን
• ድመት ወይም ውሻ ከነኩ በኃላ ወዲያውኑ እጆን መታጠብ፡፡