የታደሱ የህሙማን ማረፊያ ክፍሎች ምርቃት

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የታደሱ የህሙማን ማረፊያ ክፍሎች በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተመርቋል::

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የታደሱ የህሙማን ማረፊያ ክፍሎች እና በ326 ሚሊኒዮን ብር በመንግስት ወጪ የተገነባውና 320 አልጋዎችን የያዘው የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዛሬው እለት በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተመርቋል:: በክረምት በበጎ ፍቃደኝነት አገልግሎት ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዕድሳት የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ ባለሃብቶች እውቅና ተሰጥተዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የታደሱ ክፍሎችንና ታካሚዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝተዋል::