የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክቶቹ ሳይታዩ በቀላሉ ሊስፋፋ ይችላል ተባለ

የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክቶቹ ሳይታዩ በቀላሉ ሊስፋፋ ይችላል ተባለ
************************************************


በቻይና የተከሰተው ኮሮና ቫይረስ በታማሚዎች ላይ የበሽታው ምልክቶች ሳይታዩ በቀላሉ ሊስፋፋ እንደሚችል የአገሪቱ መንግሥት አስጠነቀቀ፡፡
ሰዎች ለቀናት ወይም ለሳምንታት ቫይረሱ እንዳለባቸው ሳያውቁ ወይም ሳይታወቅባቸው አልያም ምልክቱ ሳይታይባቸው በሽታውን በቀላሉ ሊያሰራጩ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡
ይህም የቫይረሱ አስቸጋሪ ባህሪ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት አዳጋች እንደሚያደርገው ነው የተገለጸው፡፡
እስካሁን ባለው 81 ሰዎች በዚሁ ቫይረስ መሞታቸው ተረጋግጧል።
በአሁኑ ወቅትም መነሻውን ቻይና ያደረገው የኮሮና ቫይረስ በአሜሪካ፣ ጃፓን፣ ታይላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ሲንጋፖር፣ ኔፓል እና ማሌዥያ መከሰቱ ተረጋግጧል።
ምንጭ፦ ሲኤንኤንየኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክቶቹ ሳይታዩ በቀላሉ ሊስፋፋ ይችላል ተባለ።