የድንገተኛ ሕክምና ክፍል(“ER”)
ወደ ER የሚከተሉትን ዓይነት በጣም ከባድ ችግር ሲያጋጥም ብቻ ይሂዱ፥*
– አጥንት ሲሰበር
– ደም ሲያስልዎ ወይም ሲያስታውክዎ
– የፊት፣እጅ ወይም እግር መደንዘዝ ወይም ለመናገር መቸገር
– በጽኑ በእሳት መቃጠል
– ጭንቅላት ላይ ጉዳት መድረስ ወይም ህሊናን መሳት
– ከፍተኛ ትኩሳት
– ጉዳት የደረሰበት ሕጻን
ድንገተኛ ሕክምና ክፍል
- የድንገተኛ ሕክምና ክፍል በጣም የጠና ወይም ለድንገተኛ ጽኑ ችግር ሲያጋጥም ብቻ ነው።
- ጽኑና ድንገተኛ የሆነ የጤና ችግር ሳያጋጥምዎ በድንገተኛ ሕክምና ክፍሉ ከተጠቀሙ፣ በጣም ከፍተኛ የሕክምና ወጪዎችን እንዲከፍሉ ሊደረጉ ይችላሉ