የቢጫ ወባ ወረርሽኝ

ከዚህ ከቀደም በደ/ብ/ብ/ሕ/ ክልል በጉራጌ ዞን በእነርእሞር ወረዳ የካቲት 24/2012 የቢጫ ወባ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት 86 የሚሆኑ ሰዎች በወረርሽኙ ሲያዙ የአራት ሰዎች ህይወት  አልፎዋል በኢትዩጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በክልሉ  በተሰጠው ፈጣን ምላሽ የከፋ አደጋ ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሎዋል፡፡

ይህን ተከትሎ የቢጫ ወረርሽኝ በታየበት ዞን  እና አጐራባች በሆኑት በደ/ብ/ብ/ሕ/ 11 ወረዳዎች እና በኦሮሚያ ክልል 1 ወረዳ ዳግመኛ እንደሚከሰት አመላካች ሁኔታዎች ስላሉ ከ ጥቅምት 13 እስከ ጥቅምት 19 በደ/ብ/ብ/ሕ/ ክልል በ 11 ወረዳዎች በኦሮሚያ ክልል 1 ወረዳ የቢጫ ወባ ወረርሽኝ ክትባት በመሰጠት ላይ ይገኛል ክትባቱም ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን በእነዚህ ሁለት ቀናት በታቀደው ምልኩ እየተሰጠ ነው ፡፡
የቢጫ ወባ ወረርሽኝ በተከሰተበት ዞን እና አጐራባች ክልሎች በደ/ብ/ብ/ሕ/ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ከ ስድስት ወር ጨቅላ ህፃናት ጀምሮ በሁሉም ዕድሜ ክልል ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች   ከጥቅምት 13 እስከ ከጥቅምት 19  ለክትባት በተዘጋጀ የክትባት ጣቢያ እየሄዱ እንዲከተቡ እና በክትባት ወቅት የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በጠበቀ እና የኮቪድ-19 ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ እና ከዚህም በተጨማሪም የሕብረተሰብ የጤና ስጋቶች  የሆኑ ላይ ቁጥጥር  እና ልየታ በመተሰራት ላይ ነው፡፡
የኢትዩጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማህበረሰብ ይህን በማወቅ በተዘጋጁ የክትባት ጣቢያዎች በመሄድ ክትባቱን እንዲወስድ ያሳስባል፡፡