በሀገር ዉስጥ የሚከሰት አለመረጋጋት በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት

አለመረጋጋት በአገር ዉስጥ ሲከሰት ኑሮ ይቃወሳል,  ልጆች ከቤተሰብ ይነጠላሉ,  ኢኮኖሚ በግለሰብም ሆነ በማህበረሰብ ደረጃ ይጎዳል

 የነዚህ እና የመሳሰሉት መከሰት ለተለያዩ ስነልቦናዊ ችግሮች እንዲከሰቱ መንስኤ ይሆናሉ ከነዚም ዉስጥ ጥቂቶቹ

?, Post traumatic stress disorder (PTSD)
ከጉዳት በሃላ የሚከሰት የጭንቀት በሽታ
??, የሚያስጨንቅ ሁኔታ ወይም አደጋ ከተከሰተ በሃላ የሚከሰት ከልክ ያለፈ ጭንቀት ነው

??, ከጉዳት በሃላ የሚከሰት የጭንቀት በሽታ አለ ምንለው መቼ ነው?
?, አንድ ሰው አደጋ በራሱ ላይ ደርሶበት, ሲከሰት አይቶ, ቅርቡ የሆነ ሰው ላይ መድረሱን ተረድቶ, ይህም ጦርነት, መታገት, አካላዊ ወይም ወሲባዊ ጥቃት ከደረሰ በሃላ ከስር የተጠቀሱትን ምልክቶች ሲያሳይ
- በተደጋጋሚ ክስተቱን በምናብ መሳል ወይም በህልም ማየት
- ትውስታው ሲመጣ እንደገና እንደተከሰተ ያህል መደንገጥ, ልብ ቶሎቶሎ መምታት, ማላብ, አከባቢን መርሳት
- ከሚያስታውሷቸው ነገሮች ለመራቅ መጣር, ይህም ሰው, አከባቢ, ንግግር, እቃ ሊሆን ይችላል
- ክስተቱን ሙሉ ለሙሉ ወይም ዋናዋና ነገሮቹን መዘንጋት
- ሰው ላይ እምነት ማጣት እና ከሰው መራቅ
- ራስን መውቀስ
- በፊት የሚወዷቸው ነገሮች ላይ ፍላጎት ማጣት
- ደስታ, ፍቅር የመሳሰሉት ሀሳቦችን መሰማት አለመቻል
- መበሳጨት, እንቅልፍ ማጣት
- ከ6 አመት በታች የሆኑ ልጆች ላይ ማልቀስ, አልጋ ላይ ሽንት መሽናት, መርበትበት, ከእንቅልፍ መባነን, መናገር አለመቻል ሊታይ ይችላል
?, እነዚህ ነገሮች ከ1 ወር በላይ ሲቆዩ, የለት ተለት ኑሮን ሲረብሹ እና ከመጠጥ ወይም ከሌሎች ሱሶች ጋር ካልተያያዙ ከጉዳት በሃላ የሚከሰት የጭንቀት በሽታ አለ እንላለን

Generalized anxiety disorder
ከልክ ያለፈ ጭንቀት
?, ቢያንስ ለ6ወር የቆየ ከልክ ያለፈ መቆጣጠር የሚያቅት ጭንቀት (ስለ ዓለም ሁኔታ, ቤተሰብ, ስራ, ትምህርት, አከባቢ ወዘተ) የለት ተለት ኑሮን ሲረብሽ
?,  በልጆች ላይ ደሞ
?, ረፍት ማጣት
?, ቶሎ መዳከም
?, ሃሳብ መሰብሰብ አለመቻል
?, መነጫነጭ
?, ጡንቻ ማኮማተር
?, እንቅልፍ መተኛት አለመቻል

Major depressive disorder (MDD)
ስር የሰደደ ድባቴ
??, ቢያንስ ለ2 ሳምንት የቆየ ድባቴ

??, ስር የሰደደ ድባቴ (MDD) ምልክቶች
?, በተከታታይ ለ2 ሳምንት የቆየ ድባቴ, በነገሮች አለመደሰት, ለመኖር ምክኒያት ማጣት
?, የክብደት ወይም የአመጋገብ መቀየር
?, በጣም ቁጣቁጣ ማለት ወይም መፍዘዝ
?, የጥፋተኝነት ስሜት
?, ራስን ስለማጥፋት ወይም ስለሞት ማሰብ
?, መዳክም
?, የእንቅልፍ መብዛት ወይም እንቅልፍ ማጣት
?, ለነገሮች ትኩረት አለመስጠት
??, ይህም የለትተለት ኑሮን ሲረብሽ እና ከመጠጥ ወይም ከሌላ ሱስ ጋር ካልተያያዘ
አገራችንን ሰላም ያርግልን,  ?
ጤና ይስጥልን