የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አሁንም የሕብረተሰብባችን የጤና ስጋት ነው

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ አሁንም ለብዙዎችን የጤና እክል ምክንያት በመሆኑ፡ ለታካሚዎች የተዘጋጁት የፅኑ ህሙማን አልጋዎች እና የትንፋሽ መርጃ ማሽኖች ሙሉ በሙሉ እየተያዙ መገኘት፤

ሳይመረመሩ ወይም ወደ ጤና ድርጅት ሳይሄዱ እና ምንም የሕክምና እርዳታ ሳያገኙ ትንፋሽ አጥሮት ወይም አስም ተቅስቅሶበት ሞተ የሚሉ አይነት ዜናዎች መስማት እየተለመደ መምጣት፤
•  የምናውቃቸው እና ቅርባችን የሆኑ ሰዎች በኮቪድ-19  የመያዛቸው ወይም የመሞታችውን ዜና መስማት የየዕለት ተግባራችን እየሆነ መምጣት የተለመዱ ሲሆን  
በተቃራኒው ደግሞ፡
በትራንስፖርት  መነሻና  መዳረሻ  እና  በገበያ  ቦታዎች፣ በመንግስት አገልግሎት  መስጫ  ተቋማት፣  በግል  ድርጅቶች እና  የሐይማኖት  ተቋማት  በሽታውን  ለመከላከል  እየተደረጉ  የሚገኙትን  ጥንቃቄዎች  ቀን በቀን  እየቀነሱ ወይም እየተተዉ መጥተዋል።
ይህም  በኮቪድ-19  የመያዝ  ወይም  በጽኑ ሕመም  ሁኔታን  ስለሚጨምር  የጤና ሥርዓታችን  በእጅጉ  ሊፈተን  እና  ወደ  ከፍተኛ  ችግር  ሊገባ  የሚችልባቸው  አጋጣሚዎች  ከፊት ለፊታችን  ስላለ  ሊደረስ  የሚችለውን  ሰባዊ፣ ስነ-ልቡናዊ ፣ እና  ቁሳዊ ጉዳትን  የከፋ  እንዳይሆን  እና  በሽታው  የራሳችንን ፣  የቤተሰባችንን  እንዲሁም የምንወዳቸውን  ሳይጎዳ  የሚከተሉትን  ቀላል  ነገር  ግን  እጅግ  ጠቃሚ  የሆኑ  የሚከላከሉትን  ጥንቃቄዎች እናድርግ።
•  ሁልጊዜ  በየትኛውም  ቦታ የአፍ እና የአፍንጫ  መሸፈኛ  በትክክል  ማድረጋችንን  ማረጋገጥ፣
•  ሁልጊዜ  በውሃና  ሳሙና  በመታጠብ  ወይም  በሳኒታይዘር  በማፅዳት  የእጃችንን ንፅሕና  መጠበቅ፣
•  ግዴታ  ካልሆነ  በስተቀር  ሰው  የሚሰባሰቡበት  ሁነት  ላይ አለመገኘት፣
•  በተቻለን  አቅም  በሚኖረን  እንቃስቃሴ  ሁሉትሜትር  ርቀት  መጠበቃችንን  ማስታወስ፣
•  ለመመገብ  ወይም  ለመጠጣት  ማስክ ማውለቅ  አስገዳጅ  በሆነ ጊዜ  ርቀታችንን መጠበቃችን
 እራሳችን እና ቤተሰቦቻችን ከኮቪድ -19 ወረርሽኝ እንጠብቅ፡፡