የህጻናት የደም ማነስ

የደም ማነስ ምንድን ነው?

የደም ማነስ ማለት የቀይ የደም ህዋስ ብዛት መቀንስ ሲሆን በተለይም የሄሞግሎቢን/ሄማቶክሪት ልኬት መጠን በላብራቶሪ ሲለካ ከእድሜ አቻ ህፃናት ጋር ሲነፃፀር መጠኑ የቀነሰ ሆኖ ሲገኝ ነዉ።
.
- የደም ማነስ በህጻናት እድሜ
የደም ማነስ ህጻናት ላይ በጣም የተለመደ የህመም ምልክት ነው።
.
- የደም ማነስ ለምን ህጻናት ላይ ይከሰታል?
1. ህጻናት ፈጣን እድገት ስላላቸው አንጻራዊ እጥረት ያጋጥማል
2. ከእናት በጽንስ ጊዜ ከእትብት ያከማቹት የብረት ማእድን ከ4-6 ወር ጊዜ በኋላ የሚቀንስ መሆኑ
3. ለህጻናት በተለምዶ በቤት ውስጥ የሚጀመር ምግብ በቂ የብረት ማእድን የሌለው መሆን።
.
4. ያለ በቂ ግንዛቤ ተጨማሪ ምግብ መጀመር
5. ህጻናት እያደጉ ሲሄዱ የሰውነታቸው የብረት ማእድን ፍላጎት መጨመር
6. በተፈጥሮ የብረት ማእድን ከሰውነት ጋር ያለው ውህደት አነስተኛ መሆን።
.
የደም ማነስ የህመም ምልክት እንጅ ራሱን የቻለ ህመም አይደለም። መንስኤውም እንደ እድሜ ክልል የተለያየ መሆኑ ይሰመርበት። የህመም ምልክቶቹ እንደበሽታው ክብደት ይለያያሉ። በመሰረቱ የህመም ምልክቶችን ለማሳየት መቅኔ፣ ጉበት እና ጡንቻ ውስጥ ያለው የብረት ማእድን እስኪቀንስ ድረስ ብዙ ሳምንታት የዘለቀ ጊዜ ይፈልጋል። ይህም ሰውነታችን የመጠባበቂያ የብረት ማእድን ስንቁ እስኪሟጠጥ ድረስ ከ2-3ወር የህመም ምልክቶች ላይታዩ ይችላሉ።
.
በዚህም ምክንያት የደምን የልኬት መጠን ካልወሰድን ባለሙያው በቀላሉ የሚያውቅበት እና ወላጅም የሚጠረጥርበት አጋጣሚ አነስተኛ ነው። ሆኖም ይህንን ለመቅረፍ በተለይ ለደም ማነስ የተጋለጡ እስከ ሁለት ዓመት ያሉ ህጻናትን ቢያንስ ከ3-6 ወር ባለ የጊዜ ልዩነት ሙሉ የደም ቆጠራ (CBC) በማድረግ አስቀድሞ ማወቅ ይቻላል።
.
ሌላው ግን ለደም ማነስ አጋላጭ ምክንያት ላላቸው ህጻናት ክትትል በማድረግ የከፋ የደም ማነስ ሳይከሰት ማወቅ እና ማሳከም ይቻላል። ለደም ማነስ አጋላጭ የሆኑ ሁኔታዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው።
.
- የደም ማንስ ዋና መንስኤዎች
1. የቀይ ደም ህዋስ ምርት መቀነስ
2. የቀይ ደም ህዋስ ቶሎ ቶሎ መሞት
3. የደም መፍሰስ
.
- የደም ማነስ አይነቶች
፩. ብረት ማእድን አጠር ደም ማነስ
፪. በደም ህዋስ ቶሎ መሞት የሚከሰት ደም ማነስ
፫. ውልደታዊ ደም ማነስ፡ የቀይ ደም ህዋስ ቅርጽ መጠን እና ይዘት ከተለመደው ተፈጥሮ ውጭ መሆን
፬. የቀይ ደም ህዋስ ምርት አጠር ደም ማነስ
፭. የቀይ ደም ህዋስ ግዘፍ ደም ማነስ
.
- የደም ማነስ አጋላጭ ምክንያቶች
1.በጨቅላነት እድሜ
፩. ከእትብት የደም መፍሰስ
፪. ከወሊድ በፊት የእንግዴ ልጅ መድማት
፫. ሾተላይ
፬. የእናት እና የልጅ የደም አይነት አለመመሳሰል/የእናት ደም
አይነት ኦ ሆኖ የጨቅላ ህጻን ደም ኤ ወይም ቢ ሲሆን
፭. የመወለጃ ጊዜው ሳይደርስ የተወለደ ጨቅላ ህፃን
፮. መንታ ከሆኑ ከአንድ ፅንስ ወደ ሌላኛው ፅንስ በደም ስር መወሳሰብ ምክንያት የደም መለጋገስ
፯. ተፈጥሯዊ የደም ቅርጽና መጠን መዛነፍ
.
2. በለጋነት እድሜ እና እስከ ሁለት አመት ድረስ አጋላጭ
ምክንያቶች
፩. በእርግዝና ወቅት የእናት ብረት ማእድን ማነስ
፪. የመወለጃ ቀናቸው ሳይደርስ የተወለዱ ህፃናት
፫. መንትያ ህፃናት
፬. የብረት ማእድን ያነሰው ምግብ መመገብ
፭. በምግብ እጥረት የተጎዱ ህጻናት
፮. ረጅም ጊዜ የዘለቀ ውስጣዊ ህመም
፯. የደም ካንሰር፣ የመቅኔ ህመም
፰. ያልታወቀ ረጅም ጊዜ የዘለቀ የጨጓራ ቁስለት የአንጀት ቁስለት እና የምግብ ስርገትን የሚቀንሱ ህመሞች
፱. የላም ወተት አብዝቶ መጠቀም
.
- 3. ከሁለት አመት በላይ የሆኑ ህጻናት ላይ የደም ማነስ
አጋላጭ ሁኔታዎች/ መንስኤዎች
፩. በአደጋ የደም መፍሰስ
፪. በምግብ እጥረት መቀንጨር/የብረት ማእድን እጥረት
፫. ለረጅም ጊዜ የቆየ ውስጣዊ የሰውነት ህመም
፬. የደም ካንሰር፣ የመቅኔ ህመም
፭. ደም መጣጭ የአንጀት ተዋህስያን
.
- የደም ማነስ ስሜት እና ምልክቶች
ምልክቶች እንደ ደም ማነሱ መጠን የተለያዩ ሲሆኑ ከብዙ በጥቂቱ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ይመስላሉ።
1. የድካም ስሜት
2. የፊት ማላብ
3. የሰውነት መገርጣት እና መቀንጨር
4. የምግብ ፍላጎት መቀነስ
5. የልብ ምት መፍጠን
6.ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
7. የከፋ የደም ማነስ ሲኖር የሰውነት ማበጥ ሊኖር ይችላል።
8. የፀባይ መነጫነጭ
9. የእንቅልፍ መቀነስ
10. የራስ ምታት እና ማዞር
.
‐ የምርመራ አይነት
1. ሙሉ የደም ምርመራ
2. ምክንያት ተኮር ምርመራ
3. የደም ማነስ አይነትን ለማወቅ የሚረዳ ምርመራ
4. የመቅኔን ጤንነት ለማወቅ የሚደረግ ምርመራ
- የደም ማነስ ህክምና
ህክምናው እንደ ምክንያቶች የተለያየ ሲሆን።
እጅግ የቀነስ ከሆነ ደም በመለገስ እንዲስተካከል ይደረጋል። የደም ማነሱ መንስዔው የብረት ማእድን ወይም የፎሊክ አሲድ ዕጥረት ከሆነ የሚተካውን አስፈላጊ ማእድን በመስጠት ይስተካከላል። አጋላጭ ነገሮችን/ህመሞችን ማከም/ማቆም
ይገባል።
- ስለ ደም ማነስ የተዛቡ እውነቶች
አንዳንዶች በተለምዶ ደም ማነስ የሰውነት የግፊት መጠን መቀነስ ይመስላቸዋል። ሌሎች ደግሞ ደም ማነስን ለማከም ቪምቶ ወይም ሚሪንዳ መጠቀም መፍትሔ ይመስላቸዋል።
.
- ደም ማነስን የመከላከያ መንገዶች
1. ያለ ቀናቸው ለተወለዱ እና ለደም ማነስ አጋላጭ ምክንያት ላለባቸው ህጻናት ጥብቅ ክትትል እያደረጉ ደማቸው እየታየ የብረት ማእድን እጥረት መከላከያ ፈሳሽ መድሃኒት እንዲወስዱ ማድረግ።
2. ከ4-6 ዎር እድሜ ያሉ ህጻናት የደም የሄሞግሎቢን ወይም ሄማቶክሪት መጠንን ማሰራት እና እጥረት ካለባቸው መድሃኒት እንዲውስዱ ማድረግ
.
3. ተጨማሪ ምግብ ሲጀመር በብረት እና መሰል ማእድናት እንዲበለጽግ ማድረግ
4.አንድ አመት ላልሞላው ህጻን የላም ወተት አለመስጠት። እንዲሁም የላም ወተት ሲጀምሩ በመጠን እና ልክ ማድረግ።
.
5. ከሁለት አመት በላይ የሆኑ ህጻናት ባዶ እግር እንዳይሄዱ ማድረግ እና ከ3-6 ወር ልዩነት በመደበኛነት ጸረ ወስፋት ፈሳሽ መድሀኒት መስጠት።
6.ህጻናት የሚያድጉበትን አካባቢ ከአደጋ የነጻ ማድረግ።
.
7. የትንሹ አንጀት ቀዶ ህክምና ለተደረገለት ህጻን ወይም አጥቢ እናት ሙሉ ለሙሉ ከእንስሳት ተዋጽኦ የጸዳ ምግብ የምትመገብ ከሆነ ለህጻኑ የቫይታሚን ቢ 12 መተኪያ መድሀኒት መስጠት ያድፈልጋል።