"የጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ በኢትዮጵያ"

በዚህ ፅሁፍ የጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራን እናስተዎውቃችኋለን። አገልግሎቱን ማግኘት ለምትፈልጉ በፅሁፉ መጨረሻ አድራሻ አስቀምጠናል።

ምንነቱ

- የጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ የተወሰኑት የጉልበት ክፍሎች በሰው ሰራሽ ክፍሎች ለመተካት የሚደረግ የቀዶ ህክምና ነው።
- ጉልበት በጭን አጥንት (Femur)፥ የእግር አጥንት (Tibia) እና የሎሚ አጥንት (የጉልበት እፍያ) (Patella)  መካከል የሚሰራ መገጣጠሚያ ሲሆን እነዚህ አጥንቶች እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የሚነካኩበት ቦታ ፍትጊያ ከመብዛት ወይም ከሌሎች ምክንያቶች ጋር በተያያዘ እየተበላ ሊሄድ ይችላል። በዚህም ከአቅም በላይ የሆነ ህመም በማመጣት የቀን ከቀን ኑሮን ከባድ ያደርጋል።
.
የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና
- ክብደት መቀነስ
- ፊዝዮቴራፒ በተለይም ጡንቻ ማጠንከሪያ ላይ ያተኮሩ እነቅስቃሴዎች
- የሚዋጡ፥የሚቀቡ፥ ጉልበት ውስጥ በመርፌ የሚወጉ መድሃኒቶች፤
- ጉልበት ላይ የሚታሰሩ ድጋፎች (braces) እና መሰል ህክምናዎችን መከታተል
የመጀመሪያው የመፍትሄው ሂደት ነው።
.
እነዚህን ተጠቅመን ህመሙ ለውጥ ካላገኘን እና የህመም ደረጃው ኑሯችንን በአግባቡ እንድንቀጥል ካላስቻለን፥ የጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ ዘለቄታዊ መፍትሄ ይሆናል።
.
አላማው
- ህመምን ማስወገድ
- የህይወትን ጉዞ የተሻለ ማድረግ
- የጉልበትን እንቅስቃሴን እና ስራን ማስቀጠል ወይም ማሻሻል
.
ምክንያቶቹ
- የጉልበት አንጓ ብግነት (Knee Osteoarthritis)
- በጊዜው ያልታከሙ የተለያዩ ጉልበት ላይ የሚያጋጥሙ ጉዳቶች እና ስብራቶች (Injuries)
- ጉልበት ላይ የተከሰቱ እጢዎች (Tumors)
- የጉልበት መገጣጠሚያ ነቀርሳ (Tuberculous hip arthritis) እና መሰል ችግሮቹ
- ሩማቶይድ አርትራይቲስ (Rheumatoid arthritis) እና ሌሎችም
.
.
ጉልበት መገጣጠሚያ ከማሰራታችን በፊት ማወቅ ከሚያስፈልጉን ነጥቦች በጥቂቱ:
- የቆዩ ተጓዳኝ ችግሮችን ማስተካከል
(የስኳር፥ የልብ፥ ደም ግፊት፥ የጥርስ እና ሌሎች የጤና ችግሮችን መታከም)
.
- የጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ ድንገተኛ ህክምና አይደለም፤ ስለሆነም የቀን ከቀን ኑሮን አዳጋች የሚያደርግ ህመም እስካላጋጠመ ድረስ ጊዜን ወስዶ መዘጋጀት።
.
- የሚሰራበት እቃ ስሪት (ብራንድ) ለይቶ ማወቅ፤ የተቀየረው መገጣጠሚያ ረዘም ላለ ጊዜ እንዲኖር በተቻለ መጠን የሚታወቁ (አሜሪካ እና አውሮፓ ሰራሽ) መገጣጠሚያዎችን መጠቀም ረዘም ያለ የአገልግሎት ዘመን እንዲኖራቸው ያስችላል።
.  
- ጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ የአንድ ቀን ህክምና አይደለም። ስለሆነም ከሃኪምዎ ጋር በተደጋጋሚ ከቀዶ ጥገናው በፊት የዝግጅት ምክክር ማድረግ፤ ከተሰራ በኋላም ለተሳካ የማገገም ሂደት በባለሙያ የተደገፈ ፊዚዮቴራፒ እና እንቅስቃሴ መስራት ወሳኝ ናቸው። ከመሰራቱ በፊት እና ከተሰራም በኋላ ለቀሪ የእድሜ ዘመንዎ ቀዶ ህክምና በሰራው ሃኪም ክትትል ቢደረግ የሚመከር ነው።
.
- ሁሉም ሰው እንደየመልኩ የህክምና ሂደቱ እና ውጤቱ የተለያየ ነው፥ ስለሆነም ለርስዎ ስለሚያስፈልገው የመገጣጠሚያ ቅየራ አይነት እና የማገገም ሂደት ምን መምሰል እንደሚኖርበት በሚገባዎ ቋንቋ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ያስፈልጋል።
.
.
መገጣጠሚያ በሃገር የማስቀየር ጥቅሞች
- አውነተኛ መረጃ በሚረዱት ቋንቋ ማግኘት
- ከህክምናው በፊት ሆነ በኋላ አስፈላጊውን ክትትል ማግኘት
- በወገን ላይ በሰው ሃገር ይደርስ የነበረውን እንግልት ማስወገድ
- የቤተሰብ ድጋፍ ማግኘት፥ ወዳጅ ዘመድ ጎን ሆኖ ቀዶ ህክምናን ማድረግ
- ለጉዞ እና ተጓዳኝ ነገሮች የሚደረጉ ወጭን ይቀንሳል
- ከምንም በላይ ለታካሚው የሚያስፈለገውን ህክምና (personalized care) ማግኘት
.
አድራሻ፡ ሳማሪታን የቀዶ ህክምና ማእከል (መሪ ሎቄ ያለው ሰንሻይን ግቢ ውስጥ አሜሪካን ህክምና ማእከል አጠገብ)
0116680808
.
ቀጠሮ ለመያዝ ‘book now’ የሚለውን በዚህ ገጽ የከተሉ፡
? https://fb.com/DrSamiOrtho   

የምንሰራቸውን የጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራዎች ለማየት ይህን ሊንክ ይመልክቱ
https://drsamiortho.page.link/TKA2 (የቀዶ ህክምና ሂደቱን ለማየት፥ የቀዶ ህክምና ምስሎች ስላሉት ልጆች ባያዩት ይመከራል)
https://drsamiortho.page.link/TKA1 (የረጅም ጊዜ ውጤቱን ለማየት)