በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ግዜ የጤና ባለሙያዎች መብትና ግዴታዎች

ወረርሽኞች ሲነሱ የጤና ባለሙያዎች የፊት ተሰላፊ ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ

1. ለበሽታ አምጭ ተህዋስያን እና አደጋዎች የመጋለጥ
2. ለ ረዥም የስራ ሰአት ጫና፣ጭንቀት፣ ድካም እና ስራ መሰልቸት እንዲሁም ለአካላዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃቶች የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።
ይሄንንም ለመቀነስ መብት እና ሃላፊነቶችን ማወቅ አስፈላጊ ነው።

 የጤና ባለሙያዎች መብት

1. COVID-19 ታካሚዎችን የሚንከባከቡ ባለሙያዎች በስራ ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያግዙ ቁሳቁስ ለሚሳሌ ፦ Mask,glove gown, sanitizer,soap, water...ወዘተ የማግኘት ፤

2. ስለ COVID-19  ምርመራ ፣ታካሚዎችን መለያ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መንገዶች ወቅታዊ እና ሙያዊ የሆኑ መረጃዎችን እና ተከታታይ ስልጠናዎችን የማግኘት፤

3. ባለሙያዎች ራሳቸውን እንዲመረምሩ፣ ምልክቶቻቸውን እንዲናገሩ እና ህመም ሲሰማቸው በመኖሪያ ቤታቸው እረፍት የማድረግ

4. ደህንነታቸው ባልተጠበቀበት፣ ለጤናቸው እና ለህይወታችሀ አስጊ የሆኑ አሳማኝ ሁነቶች ሲያጋጥሙ በስራ ቦታ ያለመገኘት

5. በስራ ላይ COVID-19 ኢንፌክሽን ሲያጥም ተገቢውን ካሳ ፣አንክብካቤ እና ህክምና የማግኘት መብት አላቸው ።

የጤና ባለሙያዎች ሃላፊነት

1. የሌሎች ታካሚዎችን ጤና እና ደህንነት ለመጠበቅ ተገቢውን የስራ ላይ ጥንቃቄ እና ተግባራት ማከናወን፣

2. ታካሚዎችን ለመመርመር፣ ለመለየት እና ለመንከባከብ ትክክለኛ ፕሮቶኮሎችን መጠቀም

3.የታካሚዎችን ምስጢር መጠበቅ

4. የጥርጣሬ ውስጥ ያሉ ወይንም የተረጋገጡ COVID-19 ኬዞችን ትክክለኛውን የህብረተሰብ ጤና ረፖርት ማድረጊያ መንገድ መከተል

5.የኢንፌክሽን መከላከያ ቁሳቁሶችን በአግባቡ መጠቀም እና ማስወገድ

6. ራስን መከታተል፣ ምልክቶች ሲታዩ ራስን በለይቶ ማቆያ ማቆየት እና በቶሎ ለሚመለከተው አካል ረፖርት ማድረግ።

*paraphrased from

COVID-19 OUTBREAK: RIGHTS, ROLES AND RESPONSIBILITIES ዕF HEALTH WORKERS, INCLUDING KEY CONSIDERATIONS FOR OCCUPATIONAL SAFETY
AND HEALTH