"አካል ጉዳተኞችን አካታች ምቹ እና ዘላቂ የተሻለ ዓለም በድህረ ኮቪድ-19 እንገንባ"

በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ 29ነኛ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ28ተኛ ጊዜ ተከበረ።

በዝግጅቱም ላይ የጤና  ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ሊያ ታደሰ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እንዲሁም የተለያዩ ሚኒስቴሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ለሁለት ተከታታይ ቀናት በባህርዳር ከተማ ተከብሯል። በዝግጅቱም ላይም ለአካል ጉዳተኞች ስለ ኮቪድ-19 ግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተደርጓል እንዲሁም ስለ ኮቪድ-19 አዲሱ መመሪያ 30/2013 ማብራሪያ ተሰቷል በተጨማሪም ከዚ በፊት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አካል ጉዳተኞች እና ኮቪድ-19 አስመልክቶ የሰራቸው ስራዎች በውይይት መድረኩ ላይ ተነስቷል።
#COVID19Ethiopia