ኮቪድ 19 ወረርሽኝ በመከላከል ረገድ የሆቴሎች ኢንዱስትሪ ጫና ከፍተኛ ነው ተባለ::

ኮቪድ- 19 ወረርሽኝ   በመከላከል ረገድ የሆቴሎች ኢንዱስትሪ ከዚህ ቀደም ያደርጉ የነበረውን የበሽታውን የመከላከል ጥረት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ  ጤና ኢንስቲትዩት  ዋና  ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ በዛሬው እለት በኢንስቲትዩቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከሆቴሎች ማህበራት፣ ባለቤቶች እና ኃላፊዎች ጋር በተደረገው የጋራ ውይይት መድረክ ላይ እንዳስገነዘቡት የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ  ለመከላከል እንዲሁም በሽታው የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቀነስ እንዲቻል ሁሉም የሆቴሎች ኢንዲስትሪ ዘርፍ የሆኑ ተቋማት በሙሉ ከዚህ ቀደም ሲያደርጉ የነበረውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ  የመከላከል ፕሮቶኮሎች በመተግበር የዜግነት ግዴታን  እና ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው በአሁኑ ወቅት ወረርሽኝኙ  በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተንሠራፋ በመምጣቱ እንደ ሌሎች ሁሉ  መላውን  ህብረተሰብና  የሆቴልን  ኢንዲስትሪ  ዘርፍ የሚጎዳው በመሆኑ የመከላከል ሥራን ማጠናከርና መተግበር ወሳኝ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡
በዕለቱ ልዩ ልዩ ፅሁፎች በባለሙያዎች ቀርበው ውይይቶች ተካሄደውባቸዋል፡፡