የቆዳ መሸብሸብ

የቆዳ መሸብሸብ ተፈጥሮዕዊ የሆነ የዕድሜ መጨመር ሂደት ምልክት ቢሆንም ያለ ጊዜዉ ሊፈጠር ይችላል፡፡

በተለይ ለፀሀይ የተጋለጡ የቆዳ ክፍላችን ላይ ጎልቶ ይታያል ፡፡
ለምሳሌ እንደ ፊት፣ አንገት እና እጃችን ላይ የቆዳ መሸብሸብ ይስተዋላል፡፡ በተለይም የአፍ ፣የአይንና የአንገት ቆዳ አከባቢ የተለመዱ ቦታዎች ናቸው፡፡
?የቆዳ መሸብሸብ እንዴት ይከሰታል
ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ ቆዳችን የሚያመርተው ኮላጅን (collagen) እና ኢላስቲን (elastin) የተባሉት ፕሮቲኖች እየቀነሱ ይሄዳሉ፡፡ ይህም ቆዳችን ዉሃ የመያዝ አቅም መቀነስ እና መሳሳት እንዲሁም የተለያዩ ዉጫዊ ጉዳቶችን የመቋቋም ችሎታውን እንዲቀንስ ይዳርገዋል፡፡
?የቆዳ መሸብሸብ ምክንያቶች
ተፈጥሮዕዊ ሂደት ቢሆንም የቆዳ መሸብሸብ እንዲከሰት የሚዳርጉት ምክንያቶች አሉ፡፡ እነዚህም በተፈጥሮ ተጋላጭነት፣ ከመጠን በላይ የሆነ የፀሀይ ብርሀን መጋለጥ፣ በቂ ዉሃ ያለመጠጣት፣ የአየር ብክለት ብናኝ፣ ሲጋራ ማጤስ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
?የቆዳ መሸብሸብን እንዴት እንከላከል
የቆዳ መሸብሸብን ለማዘግየት ከሚያስችሉ ነገሮች አንዱ የጸሀይ መከላከያ ቅባት መጠቀም ነዉ። የጸሃይ መከላከያ ቅባት ወይም sun screens ተብለዉ የሚታወቁትን ከመድሃኒት መደብር ገዝተዉ መጠቀም ይችላሉ። የእያንዳንዱ ሰዉ ቆዳ ስለሚለያይ የተለያየ ሰዉ የሚያስፈልገዉ የጸሃይ መከላከያ ስለሚለያይ መጀመሪያ የቆዳ አይነትዎን በምርመራ መለየቱ ይመከራል።