የልጆች የሳምባ ምች(ኒሞኒያ) ምንድነው?

ሳምባ ምች(ኒሞኒያ) ማለት የሳምባችን የታችኛው እና የመጨረሻው ክፍል መቆጣት እና መታመም ነው:: እንደሚታወቀዉ ሳምባችን ለሰውነታችን ኦክስጅን የሚባለውን ጠቃሚ አየር የምናስገባበት እና ካርቦንዳይ ኦክሳይድ የሚባለውን የተቃጠለ አየር የሚናስወግድበት አካላችን

ሲሆን ይህ አካል ደሞ ኒሞኒያ በሚባለው በሽታ ሲጠቃ ሳምባችን ዉስጥ ያሉ ህዋሳት በከፍተኛ መጠን ስለሚቆጡ አየር የሚቀያየርበት የሳምባ ቅንጣት አካላት(Alveolus) በፈሳሽ ነገር ይሞላል በዚህም ምክንያት ሰውነታችን በቂ የሆነ ኦክስጅን አያገኝም:: የልጆች ሳምባ ደሞ በደምብ ያልዳበረ እና ጠባብ ስለሆነ በወቅቱ ካልታከመ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል::
እንደ ዓለም የጤና ድርጅት(WHO) መረጃ መሰረት በ2017 ብቻ በዓለም ላይ 808,694 እድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት በሳምባ ምች ምክንያት ህይወታቸውን አተዋል:: ይህም ከአጠቃላይ የልጆች ሞት 15% ይይዛል ::

ሳምባ ምች(ኒሞኒያ) መንስኤው ምንድነው?
ይህ በሽታ ብዙ ጊዜ በአይን በማይታዩ የበሽታ አምጭ ጀርሞች ማለትም በቫይረስ, በባክቴርያ, በፕሮቶዝዋ አልፎ አልፎም በፓራሳይት አማካኝነት ሊመጣ ይቻላል:: ከነዝህም ዉስጥ በአብዛኞቹ ጀርሞች በሳል ወይም በንጥሻ ወቅት በትንፋሽ የሚተላለፉ ናቸው:: ከነዚህ በሽታ አምጭ ጀርሞች በተጨማሪም ኒሞኒያ በተለያዩ ኬሚካሎችም ሊመጣ ይቻላል::ለምሳሌ የጨጓራ አሲድ በድንገት ወደ ሳምባ ከገባ ኒሞኒያ ሊያስከትል ይችላል:: ከ 5 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ላይ የሳምባ ምች ብዙ ጊዜ መንስኤው ቫይረሶች ሲሆኑ የሚጀምረውም ከጉፋን መሰል ምልክቶች ነው::

ልጆችን ለሳም ባምች(ኒሞኒያ) የሚያጋልጡ ነገሮች
1.የላይኛው የትንፋሽ አካላት ኢንፌክሽን ለምሳሌ ጉፋን፤ የቶንሲል ኢንፌክሽን እና የመሳሰሉት
2. ቤት ዉስጥ የሚጨሱ ማንኛዉም የጭስ አይነቶች ለምሳሌ የሲጋራ የከሰል እና የእንጨት ጭሶች በሀገራችን በከፍተኛ መጠን ብዙ ህፃናትን ለሳምባ ምች እያጋለጣቸው ይገኛል::
3. ዝቅተኛ የበሽታ መከላከል አቅም(በምግብ እጥረት ወይም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት)
4. በጣም ተጠጋግቶ መኖር እና በቂ የሆነ የአየር ዝውውር በሌለበት ቤት እና አካባቢ መኖር
5. የሳምባ የተፈጥሮ ችግሮች
6. የቫይታሚን ዲ እጥረት(ሪኬትስ)፦ በተለይ ፀሐይ በደምብ ያልሞቁ ህፃናት ለሳምባ ምች ተጋላጭ ናቸው::

ምልክቶቹ ምንድናቸው?
• ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
• ትንፋሽ ማጠር እና ለመተፈስ መቸገረ
• ትኩሳት
• ማቃሰት
• ትውከት
• የደረት ውጋት ወይም ህመም
• ህፃናት ሲተነፍሱ የታችኛው ደረት ክፍል ወደ ዉስጥ ግብት ግብት ማለት ናቸው::
• ልጆት ላይ እነዚህ የተጠቀሱት ምልክቶች ካሉ ባፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መውሰድ እና ማሳከም ይኖርቦታል::
ልጆች ሳምባምች(ኒሞኒያ) እንዳይዛቸው ምን እናድርግ መከላከያ መንገዶችስ ምንድናቸው?
• ክትባት
• ቤት ዉስጥ ማንኛዉም ጭስ አለማጨስ
• ቤት ዉስጥ በቂ የ አየር ዝውውር እንዲሮር ማድረግ
• የተመ ጣ ጠ ነ ምግብ መመገብ
• እስከ 6 ወር ያሉ ህፃናት የእናት ጡት ወተት ብቻ እንዲወስዱ ማድረግ
• ልጆች የፀሀይ ብርሃን በበቂ ሁኔታ እንዲያገኙ ማድረግ
• ልጆችን ጉፋን ከያዛቸዉ ሰዎች በተቻለ መጠን ማራቅ ይገባል::