እንደ ስጋ አይነት ነገር በአየር ቧንቧ ውስጥ ተሰንቅሮ ካጠገባችን ቢያጋጥመን ምን ማረግ አለብን?

አልፎ አልፎ ቢሆንም በተለይም በዓላት ጊዜ ስጋ ወይንም እንደ ስጋ አይነት ነገር በአየር ቧንቧ ውስጥ ተሰንቅሮ ካጠገባችን ቢያጋጥመን ምን ማረግ አለብን? እንደዚህ አይነት አደጋንስ እንዴት እንከላከለዉ?

በዋናነት ምግብ ስንበላ የአምጋገብ ስርዓት በጠበቀ መልኩ ማድረግ በደንብ ማላመጥና አለማዉራት እንዲሁም አላስፈላጊ እንቅስቃሴ ያለማረግና ከተቻለም ሀምሊች ማኑቫር መጠቀም አለብን። እንዴት መደረግ እንዳለበትም በሚከተለው መልኩ ተቀምጧል
.
1. ከተሰነቀረብት ሰዉ ጀርባ መሆን
2. በመቀጠልም ሁለቱም እጆቻችንን በእንብርትና ጎዲን አጥንት መሃል ማረግ
3. ሁለተኛው እጃችን በመጀመሪያው ላይ ማሳረፍና (መደረብ) በመጨረሻም በሁለተኛው እጃችን በደንብ መጫን በቂ አየር ከዉስጥ እስኪመጣ ድረስ
4 ለዉጥ ከሌለ (ካልወጣ) መደጋገም።
.

ዶ/ር ሙባረክ ዘይኑ ፤ የድንገተኛና ፅኑ ህሙማን ሬዚደንት