የጨቅላ ህፃናት አደገኛ ምልክቶች? የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?

የጨቅላ ህፃናት አደገኛ ምልክቶች? የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?

? ጡት አለመጥባት ወይም መጥባት መቀነስ
? ቶሎ ቶሎ መተንፈስ( በደቂቃ ከ 60 በላይ የሚተነፍስ ከሆነ)
? ረጅም ሰዓት የሚቆይ ማቃሰት
? የሰውነት ትኩሳት ከ 38 ሴንቲግሬድ በላይ ከሆነ
? የሰውነት በጣም መቀዝቀዝ ከ 35.5ሴንቲግሬድ በታች ከሆነ
? የሰውነት መንቀጥቀጥ
? በጣም ተከታታይ እና ኃይለኛ ትውከት
? የአይን እና የሰውነት ቢጫ መሆን
? በጣም መፍዘዝ እና አለመንቃት ወይም ራስን መሳት
? የከንፈር እና የምላስ መጥቆር
? የሆድ ከመጠን በላይ መነፋት
? በተወለደ በ48 ሰዓት ዉስጥ ካካ ካላለ
? በተወለደ በ24 ሰዓት ውስጥ ሽንት ካለሸና

⚠️ ወላጆች ከላይ ላይ የተገለፁት ምልክቶች ካሉ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድ ይኖርባችዋል ማለት ነው ::