የእግር ላይ ህመም አለዎት?

የእግር ላይ ህመም  ፣ የእግር ጣቶች መጣመም፣ ወይም ከወትሮዉ  የተለየ ስሜት ካጋጠመዎ ወይም ካለዎ እያደረጉ ያለዉን የእግር ጫማዎን መጠን በትክክል እንደሚሆነዎና እንደማይሆንዎ ያረጋገጡ።  በ2018 በተደረገ አንድ ጥናት  ትክክለኛውን ርዝመት እና ስፋት ያላቸውን ጫማዎች  የሚያደርጉት ከ28 እስከ 37% የሚሆኑት  ሰዎች  ብቻ ናቸዉ።

በትክክል የማይሆንዎ የጫማ መጠን ማድረግና  የጤና ችግሮቹ

1. የእግር ህመምና መጣመም
በትክክል የማይሆንዎ ጫማ ማድረግ ለእግር ህመምና ለእግር ጣቶች መጣመም ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል።  አንድ አንድ ጊዜ የጫማዎ ቁጥር ትክክል ቢሆንም የሚያደርጉት የጫማ ቅርጽ ከእግርዎ ቅርጽ ጋር የማይስማማ ከሆነ ተመሳሳይ ችግር ሊያመጣ ይችላል። ቀደም ሲል የእግር ጣቶች መጣመም ችግር ካለብዎ ለስላሳ ቅርፅ ያላቸው ጫማዎች ቢጫሙም  ባልተስተካከለ ቅርጽ ባላቸው የአጥንት ቦታዎች ላይ ጫና እንዲፈጥር የማድረግና ችግሩ እንዲባባስ የማድረግ አቅም አለዉ።

2. የነርቭ ችግር
ይህ እግርዎ ላይ የመጠቅጠቅ እና የመዉጋት ስሜት እንዲሁም የመደንዘዝ ባህሪ እንዲኖር የሚያደርግ ሲሆን ጉዳቱ አንዴ ከተፈጠረ መልሶ የማገገመ እድሉ አነስተኛ ነዉ።

3. የእግር ጣት ጥፍር ወደ ዉስጥ ማደግ
የእግር ጫማዎ ጠባብ ወይም አጭር ከሆነ በእግር ጣትዎ ላይ በሚፈጥረዉ ተጨማሪ ጫና  የጥፍርዎ ጫፍ ወደ ቆዳዎ ዉስጥ እንዲበቅል ያደርጋል።  ወደዉስጥ ያደገዉ ጥፍር ደግሞ በጥፍር ዙሪያ ያለዉን ቆዳ እንዲቆጣና ኢንፌክሽን እንዲፈጥር ያደርጋል። ይህ ችግር በአብዛኛዉ በእግር አዉራ ጣት ላይ የሚከሰት ቢሆንም በሌሎች የእግር ጣት ጥፍሮች ላይም ሊከሰት ይችላል። ይህንን ችግር ለማስቀረት በትክክል የሚሆነዎን  ጫማዎች ማድረግዎን  ያረጋግጡ ፥ በተጨማሪም  ጥፍሮችዎን ሲቆርጡ በጣም አጭር ወይም ጠርዙን ክብ አያድርጉ።

4. የአኗኗር ጥራትን ይቀንሳል
ጫማዎ ያለማቋረጥ እግርዎን የሚጎዳ ከሆነ ቀሪው የሕይወትዎን ዘመን በዚህ ጉዳት መሰቃየትዎ አይቀርም፡፡ በተጨማሪም በትክክል ከማይሆንዎ ጫማ ጋር የተዛመዱ የእግር ህመምና ሌሎች የእግር ጉዳቶች  እንደ የመውደቅ ፣ የመንቀሳቀስ አቅምን የመቀነስ እንዲሁም  በዕድሜ የገፉ አዋቂዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን በነፃነት ራስን ችሎ መንቀሳቀስ የመቀነስ ችግርን  ሊያስከትል ይችላል።

5.  የጫማዎ መጠን መለዋወጥ
ብዙ ሰዎች አንድ ሰዉ ዕድሜዉ 18 ዓመት ከሞላዉ ወይም አካላዊ እድገቱን ከጨረሰ የእግሩ መጠን አይለወጥም ብለዉ ያስባሉ። ነገር ግን በህይወት ዘመንዎ እግሮችዎ በብዙ መንገዶቸ ይለወጣሉ፤
• እድሜዎ እየጨመረ ሲሄድ ጅማቶች ስለሚላሉ እግርዎ በተፈጥሮ እየሰፋ ይሄዳል፤
• የተወሰኑ ህመሞችና መድሃኒቶች ዉሃ ከሰዉነት እንዳይወገድ ስለሚያደርጉ የእግር እብጠት እንዲከሰት የደርጋሉ።
• በእርግዝና ወቅት በሆርሞን መለዋወጥ ምክንያት እግር እብጥት ስለሚከሰት የእግር መጠን እንዲጨምር ያደርጋል።
በወጣቶቸ ላይም ቢሆን ወደማታ መጠነኛ የሆነ የእግር እብጠት ሊታይ  ይችላል። በተለይ  ለረጅም ጊዜ መቆም ካለ፤ ከረጅመ የእግር ጉዞ ፣ ሩጫ ወይም እስፖርታዊ እንቅስቃሴ  በኃላ እብጠት ሊታይ ይችላል።
ይህ ማለት ጧት ለስራ ወይም ለእንቅስቃሴ ሲወጡ በትክክል ይሆንዎ የነበረ ጫማ ወደአመሻሽ ወይም እንቅስቃሴ ከጨረሱ በኃላ ሊጠብዎ ይችላል።

የጫማ መጠኑ ትክክል አለመሆኑን የሚያመለክቱ ነገሮች
ህመምና ምቾት ማጣት ካለ  ጫማዎ በትክክል እየሆንዎ እንዳልሆን  ማሳያ ምልክቶች ናቸዉ። ከሚከተሉት ነገሮች ካሉ የጫማዎን ሁኔታ ማጤን መጀመር እንዳለብዎ ያሳያል፦
• በእግር  ጥፍርዎ ላይ መጫጫር፣መቅላት አሊያም መልክ መቀየር  ካለ
• የእግር ጣት ጥፍር መነሳት፣ መነቀል ወይም መጎዳት ካለ
• ዉሀ የቋጠር ካለ
• በእግር ጥፍር ዙሪያ ያለዉ ቆዳ መቆጣት ካለና
• የእግር ቆዳ ( በመርገጫ በኩል)  መደደር ወይም መጠንከር ከመጣ ናቸዉ።