የማህፀን ፈሳሽ

የማህፀን ፈሳሽ ሴቶች ወደህክምና ተቋማት እንዲሄዱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ ነው።

 የማህፀን ፈሳሽ ጤናማ የሆነ ና ጤናማ ያልሆነ ብለን ልንከፍለው እንችላለን።
ጤናማ የማህፀን ፈሳሽ ብዛት የሌለው በቀን ከ 2-4 ሚሊ ሊትር የሚደርስ ነፃ ያለ ፣ ሽታ የሌለው ነው።
• መጠኑ ፣ከለሩና ውፍረቱ ከ ሴት ሴት ሊለያይ ይችላል።

መጠኑ እንዲጨምር ከሚያደርጉ ጤናማ ምክንያቶች መካከል
• እርግዝና
• የእርግዝና መከላከያ እንክብል (ፒልስ) መጠቀም
• የወር አበባ ከታየ በኋላ በ14ኛው ቀን አካባቢ እና የወር አበባ ሊመጣ ሳምንት ሲቀረው ይገኙበታል።
ጤናማ ያልሆነ የምንለው የሚከተሉት ተያያዥ ምልክቶች ሲኖሩ ነው
• ማሳከክ
• ማህፀን አካባቢ መቅላት፣ማቃጠል እና እብጠት
• አረፋ የመሰለ አረንጓዴ /ቢጫ ፈሳሽ
• መጥፎ ጠረን ካለው
• ደም ከቀላቀለ
• በግንኙነት ወቅት ህመም ካለ
እነዚህ ተያያዥ ምልክቶች ካሉ የጤና ባለሙያ ማማከር ተገቢ ነው።

• በተለያየ ባህላዊ መንገድ ወይም በራስ ተነሳሽነት ለማከም መሞከር ሁኔታውን ሊያባብስ ስለሚችል አይመከርም።

ጤናማ ያልሆነ ፈሳሽ እንዳይከሰት ምን ማድረግ ይቻላል?
• በንፁህ ውሀ ወይም ሽታ የሌለው ሳሙና በመጠቀም የውጨኛው የብልት ክፍል መታጠብ ( የገላ መታሻ ወይም ጓንት መጠቀም አያስፈልግም)
• ብልትን ወደ ውስጥ ገብቶ አለመታጠብ
• ለብልት ንፅህና መጠበቂያ ተብለው የሚመረቱ ስፕሬይ ፣ፓውደር ወይም ፈሳሽ ምርቶችን አለመጠቀም
• ከጥጥ የ ተሰራ ፓንት መጠቀም
• ከተፀዳዱ በኋላ በውሀ መታጠብ ሶፍት ወይም ዋይፕስ(baby wipes ) አለመጠቀም
#ለሌሎች_ሸር_ያድርጉት