ብዙ ፈሳሽ የቋጠረ የኩላሊት ህመም (Polycystic kidney disease)

በዘረ መል የሚመጣ  በኩላሊት ላይ ብዙ ውሀ የቋጠሩ እጢዎች እንዲወጣ የሚያደርግ ችግር ነው።

ይህ ህመም የኩላሊት ቅርፅ እንዲቀየር እና መጠኑ እንዲጨመር ያደርጋል።

Polycystic kidney disease የረጅም ጊዜ የኩላሊት በሽታዎች አንዱ ሲሆን የኩላሊትን የመስራት ችሎታ ይቀንሳል ለኩላሊት መድከምም ያጋልጣል።

ከዚህ በተጨማሪም የደም ግፊት ያስከትላል ፣ በጉበት ላይ ውሀ መቋጠር ሊፈጥር ይችላል ፣ የአንጎል እና የልብ የደም ቧንቧ ችግርም ይፈጥራል ።

የሆድ፣የሽንጥ እና የጀርባ ህመም ዋነኛ ምልክቱ ነው።
#ለሌሎች_ሸር_ያድርጉት