ካንሰር እንዴት ይከሰታል ?

ካንሰር በማንኛውም የሰውነት አካል፣ ቲሹ ወይም ህዎሶች ውስጥ ሊጀምር የሚችል ከትላልቅ የህመም አይነቶች ዉስጥ የሚመደብ የህመም አይነት ነው።

ካንሰር የሰዉነታችን ሴሎች ወይም ህዋሶች ባልተለመደና ከቁጥጥር ዉጪ በሆነ  ሁኔታ ሲያድጉ ፣ ከተለመደው ድንበራቸው አልፈው በአጠገባቸዉ ያሉትን የአካል ክፍሎችን ሲወርሩና እንዲሁምም ወደ ሌሎች አካላት ሊሰራጭ የሚችል ነዉ። ይህ የካንሰር ወደ ሌሎች የሰዉነት አካላት የመሰራጨት ሂደት የካንሰር መሰራጨት ወይም ሜታስታሳይዝ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በካንሰር ምክንያት ለሚከሰት ሞት ዋነኛው መንስኤ ነው ፡፡

ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሞት ከሚዳርጉ ህመሞቸ መካከል  በሁለተኛ ደረጃ የሚገኝ ሲሆን በዓለማችን  እኤአ በ2020 ብቻ በዓለማችን ለአስር ሚሊዮን ሰዎች ሞት ምክንያት ነበር። የሳንባ፣ የፕሮስቴት፣የትልቁ አንጀት የጨጓራና የጉበት ካንሰር በወንዶቸ ላይ በብዛት ከሚከሰቱት የካነሰር አይነቶች ሲመደቡ በሴቶች ላይ በብዛት ከሚከሰቱት ዉስጥ ደግም የጡት፣ የትልቁ አንጀት፣ የሳንባ የማህፀን ጫፍና የታይሮይድ ካነሰሮች ይገኛሉ።

ካንሰር እንዴት ይከሰታል
ካንሰር የሚነሳዉ ጤነኛ የሰዉነታችን ሴሎች በብዙ ደረጃ፣ ሂደትና ለዉጥ ወደ ጤናማ ያልሆኑ ወይም ቲዩመር ሴሎች የሚለወጥበትና ከዚያም  ወደ ቅድመ ካንሰር ሴሎችና በሂደት ወደ ካንሰር ሴሎች የሚሸጋገርበት ነዉ። እነዚህ ለውጦች በአንድ ሰው ተፈጥሮዊ ስሪቱ( ጄኔቲክ)ና በሶስት ከሰዉነት ዉጪ በሆኑ ከሚከተሉት  መንስኤዎች መካከል ባለዉ መስተጋብር ውጤት የሚከሰት ነዉ። እነርሱም፦
#አካላዊ የካንሰር አምጭዎች፥ የፀህይ ጨረርና አዮናይዚንግ ራዴሽን( ጨረር)
#ኬሚካል የካንሰር አምጪዎች፦ አስቤስቶስ፣ ሲጋራ፣ አፍላቶክሲን ( ምግብምን የሚበክሉ)፣ አርሰኒክ( የሚጠጣ ዉሃን የሚበከሉ) እና
#ባዮሎጂካል የካንሰር አምጪዎች፦ በቫይረስ፣ በባክቴሪያና በፓራሳይት አማካኝነት የሚከሰቱ እንፌክሽኖች ናቸዉ።

ለካንሰር ሊያጋልጡ የሚችሉ መንስኤዎች ምንድናቸው?
#ሲጋራ ማጨስ
#አልኮሆል
#ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ስርዓት
#የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ
#የአየር መበከልና
#ስር የሰደዱ ኢንፌክሽኖች ፦ ለምሳሌ የጨጓራ ባክቴሪያ፣ የጉበት ቫይረስ “ቢ”፣ የጉበት ቫይረስ “ሲ”፣ ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስና ኢፒስቴይን ባር ቫይረስ የመሳስሉት ናቸዉ።

የካንሰርን ጫና መቀነስ
በአሁኑ ጊዜ ከ 30 እስከ 50% የሚሆኑ ካንሰሮችን ለካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ሁኔታዎች በማስወገድና  በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ የመከላከያ ስልቶችን በመተግበር መከላከል ይቻላል ፡፡ ካንሰርን አስቀድሞ  በመመርመር( አጠቃላይ ምርመራ በማድረግ) እንዲሁም በካንሰር ለተያዙ ህመምተኞች ተገቢውን ህክምና እና እንክብካቤ በመስጠት የካንሰር ጫናን መቀነስ  ይችላል። ቀደም ብለው ከተመረመሩና ተገቢዉን ህክምና ካደረጉ ከብዙ ካንሰሮች የመፈወስ  እድል ከፍተኛ ነው ፡፡
ካንሰርን መከላከል
የካንሰር ተጋላጭነትን ለመቀነስ
#ሲጋራ አለማጨስ ወይም እያጨሱ ከሆነ ማቆም
#ጤናማና የተስተካከለ የሰዉነት ክብደት እንዲኖርዎ ማድረግ
#አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ ጤናማ አመጋገብ እንዲኖርዎ ማድረግ
#መደበኛ በሆነ መንገድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
#አደገኛ የአልኮል መጠጥን ከመጠቀም መቆጠብ  
#የማህፀን አንገት ካንሰርና የጉበት ካንሰርን ለመከላከል ክትባት መዉሰድ
#ከአለትራቫዮሌት ጨረር ተጋላጭነትን መቀነስ
#ከስራ ጋር ወይም ከህክምና ጋር በተያያዘ  የአዮናይዚንግ ራዴሽን ተጋላጭነትን መቀነስ
#ከቤት ውጭ ብክለትና በቤት ውስጥ ከሚከሰት የአየር ብክለት ተጋላጭነትን መቀነስ