5 ፊታችን ማስነካት የሌለብን ነገሮች

1. ሎሚ : ሎሚ ፊት ላይ ማድረግ አደገኛ ነው ምክንያቱም ሎሚ ውስጥ ያለው ሲትሪክ አሲድ የአሲድ መጠኑ ደረጃ ከ2-3 ሲሆን የቆዳችን የኬሚካል አሰራር ደግሞ የአሲድ መጠኑ ከ4-4.5 ነው ።

ስለዚህ የሰውነት ቆዳ ሎሚ ከተቀባ ሊጎዳ ይችላል በተለይም ተቀብቶ ወደፀሀይ ከወጡ ቆዳዎን ሊያቃጥለውና ጠባሳ ሊፈጥር ይችላል ። ሎሚ የሚጠቀሙ ከሆነ የሚከተሉትን ማድረግ የተሻለ ነው ።
1. ማቅጠን አለብዎት በንፁህ ውሀ
2. አድስ (fresh) ሎሚ ይጠቀሙ
3. ከተጠቀሙት በኋላ ሳይታጠቡ ለፀሀይ አይጋለጡ ።

2. ቫዝሊን ( Vaseline ) - በጣም ሀይለኛ የሆነ ቅባት (fat) ያለውና በሰውነት ቆዳ ላይ ያሉ ባክቴሪያዎችን እና ፈንገሶችን በመሸፈን ከመጠን በላይ እንዲራቡና የተለያዩ በሽታዎች ቡግርን ጨምሮ እንዲያመጡ ሊያደርግ ይችላል ። ከዚህም በተጨማሪ የሰውነት ቆዳ ቀዳዳዎችን እንዲደፈኑ በማድረግ ብዙ የቆዳ እብጠቶች ያመጣል ። በተለይም  ለቡግር ተጋላጭና ቀላ ያለ የቆዳ እብጠት  ካለ ቫዝሊንን መጠቀም ያቁሙ ።

3. የመጋገሪያ እርሾ ( baking soda ) እና ዱቄት ሳሙናዎች (washing soda) _ እነዚህ ሁለቱ ከsodium carbonate የሚሰሩ ሲሆን በውሀ በሚሟሙበት ጊዜ ደካማ የአልካላይን ኬሚካል ናቸው ። ቆዳ ደግሞ የደካማ አሲድ ኬሚካል ፀባይ ነው ያለው ። ስለዚህ ይህን የሚጠቀሙ ከሆነ የሰውነት ቆዳ የኬሚካል አሰራር ሁኔታ እየቀየሩ ነው ማለት ነው። የሰውነት ቆዳ የኬሚካል ለውጥ ካለው ደግሞ ለተለያዩ በሽታዎች ይጋለጣል ።

4. የጥርስ ሳሙና (toothpaste )- የጥርስ ሳሙና ቆዳን irritate የሚያደርግ ፣ የሚቧጥጥና የሚያቀላና የቆዳ መቆጣት የሚያመጡ የተለያዩ ኬሚካሌች አሉት ። በተጨማሪም የቆዳ ድርቀትን በማምጣት ወዝ የሚያመርቱ ሴሎችን ከመጠን በላይ ወዝ እንዲያመርቱ ሊያደርጋቸው ይችላል ።

5. አልኮል ያላቸው ቅባቶች- አልኮል ያለቸው ቅባቶችና የፊት መጥረጊያዎችን መጠቀም የቆዳ ድርቀት ያመጣል ። በተደጋጋሚ የሚጠቀሙ ከሆነ የቆዳ ድርቀትን ለመከላከል ሲል ወዝ የሚያመርቱ ሴሎች ከፍተኛ የሆነ ወዝ እያመረቱ ይመጣሉ ይህም ከፍተኛ የሆነ ወዝ በሰውነት ላይ እንዲመረት በማድረግ ሊረብሽ ይችላል ።