ጤናማ እንቅልፍ እንዴት ማግኘት እንችላለን?

ሰውነትዎን እና አእምሮዎን ጤናማ ለማድረግ በቂ እንቅልፍ መተኛት ወሳኝ ነው፡፡ የእንቅልፍ ፍላጎእንደ ዕድሜ ይለያያሉ፡፡

የአሜሪካ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ የሚከተሉትን የእንቅልፍ መመሪያዎች ይመክራል፡፡

• አዋቂዎች ከ 7 እስከ 8 ሰዓታት ያስፈልጋቸዋል፡፡
• ወጣቶች ከ 8 እስከ 10 ሰዓታት ያስፈልጋቸዋል ፡፡
• ዕድሜያቸው ለትምህርት ያልደረሱ ልጆች ከ 10 እስከ 13 ሰዓታት ያስፈልጋቸዋል ፡፡
• ታዳጊዎች ከ 11 እስከ 14 ሰዓታት ያስፈልጋቸዋል ፡፡
• ሕፃናት ከ 12 እስከ 16 ሰዓታት ያስፈልጋቸዋል ፡፡

ጥሩ የለሊት እንቅልፍ እንደሚከተለው ሊገለፅ ይችላል?
• በቀላሉ መተኛት
• በሌሊት ሙሉ በሙሉ አለመንቃት
• በሚጠበቅብን ሰአት መንቃት (ጠዋት)
• ጠዋት ላይ የመታደስ ስሜት
• ፈካ ያለ እንቅልፍ የሚተገኙ ከሆነ
ጥሩ እንቅልፍ የማያገኙ ከሆነ
• በሽታ የመከላከል አቅምዎ ይቀንሳል
• ለልብ ህመም ተጋላጭ ያደርጋል
• የአእምሮ የመስራት አቅም ይቀንሳል
• ለጭንቀት ተጋላጭ ይሆናሉ
• ለክብደት መጨመር ያጋልጣል
• የሰውነት የደም ስኳር የመቆጣጠር አቅም ያዳክማል
• ጥሩ ተግባቦት (mood) አይኖርዎትም
እንቅልፍ ማጣት (Insomnia )
1. እንቅልፍ አልወስድ ማለት
2. ለብዙ ሰዓት ተኝቶ መቆየት አለመቻል
3. በጊዜ መንቃት

የእንቅልፍ ማጣት ምክንያት
1. በራሱ እንደችግር የሚቆጠር ( primary )
2. ሌሎች እንቅልፍ ማጣት የሚያመጡ ችግሮች ያሉት - ድባቴ ፣ የተለየ ሰዓት አቆጣጠር ያለበት ቦታ በረራ ፣ አነቃቂ ነገሮች መጠቀም ፣ በሚተኙበት ጊዜ የሚፈጠር የትንፋሽ መቋረጥ

ህክምናው እንደምክንያቱ የተለያየ ነው ።
የመድኃኒት ህክምናና sleep hygiene መጠበቅ ።

ጥሩ እንቅልፍ እንዴት ማግኘት ይቻላል? የሚከተሉትን ይሞክሩ…
• ከሥራ እረፍት የሚደረጉ ቀናትዎን ጨምሮ በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት ለመተኛት እና ለመነሳት ይሞክሩ
• ከመተገኛቶ በፊት ገላዎን መታጠብ ፡፡
• መኝታ ቤትዎን ዘና ፣ ጸጥ እና ጨለም ያለ ማድረግ ፡፡
• ቴሌቪዥኖችን ፣ ኮምፒውተሮችን እና ሞባይል ስልኮችን ጨምሮ ለመተኛት ሲያስቡ መጠቀም ማቆም፡፡
• መኝታ ቤትዎ እንዲቀዘቅዝ ያድርጉ/ሙቀቱን ማመጣጠን፡፡
• ከሰዓት በኋላ ወይም አመሻሽ ላይ አለመተኛት።
• በየቀኑ በመደበኛ ጊዜያት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እና ከመተኛትዎ በፊት ቢያንስ ለሦስት ሰዓታት ማረፎትን ማረጋገጥ፡፡
• ካፌን ይዘት ያላቸው ነገሮች ለምሳሌ እንደ ቸኮሌት፣ ሻይ፣ ኮካ እና ቡና ከመሸ አይውሰዱ፡፡
• ከመገኛቶ በፊት ከበድ ያሉ ምግቦችን አለመመገብ ፡፡
• ከመተኛቶ በፊት የአልኮል መጠጦችን ከመጠጣት መቆጠብ ፡፡