10 ለደም ግፊትና ለልብ ጤና ተስማሚ ምግቦች

በአለማችን በየአመቱ ከሚሞቱ ሰዎች አንድ ሶስተኛው የሞታቸው ምክንያት የልብ ድካም ነው።

የአመጋገብ ስርኣት የልብ ጤናን አደጋ ላይ ከሚጥሉ ነገሮች አንዱ ነው።አንዳንድ ምግቦች የደም ግፊትና ኮሌስትሮል መጠንን ከፍ በማድረግ ለልብ ድካም ያጋልጣሉ።

ቀጥሎ የጠቀስኳቸውን 15 ምግቦች በማዘውተር የልብን ጤና መጠበቅ ይቻላል።

1ኛ፦የጓሮ አትክልት በተለይ አበባባ ጎመን (broccoli )
የጓሮ አትክልቶች በአጠቃላይ ከፍተኛ የናይትሬትና የቫይታሚን ኬ መጠን ስላላቸው የደም ግፊት እንዳይጨምር በማድረግ የልብ ድካምን እንደሚከላከሉ በርካታ ጥናቶች አሳይተዋል። እነዚህ ምግቦች በብዛት የሚገኙና በአነስተኛ ዋጋ ያሉ ቢሆንም ብዙ ሰዎች ሲያናንቋቸው ማየት የተለመደ ነው። የልቡን ጤና የሚፈልግ ሰው ግን ቢወዳቸው መልካም ነው።

2ኛ፦ሰትሮቤሪስ (እንጆሪ)
እንጆሪ በአንቲ ኦክሰዳን የበለፀገ በመሆኑ ከሰውነት ብግነት(inflammation ) እንዲሁም ከኮሌስትሮል በመከላከል የደም ግፊትና የልብ ድካም እንዳይገጥን ይረዳል።

3ኛ፦ አቦካቶ(avocados)
አቦካቶ የጥሩ ቅባት ምንጭ ሲሆን መጥፎ ቅባትን በመቀነስና የፖታሺየም መጠንን በመጨመር ለልብ ምቹ ከሆኑ ምግቦች ተርታ ከቀዳሚዎቹ ይሰለፋል። በተጨማሪም የደም ግፊት እንዳይዘን ይረዳል ።

4ኛ፦ኣሳ(Fish) እንደ ሳልመን፣ሳርዲንና ቱና ያሉ የአሳ ምግቦች ከፍተኛ የ ኦሜጋ-3 ቅባት(ጥሩ ቅባት) ስለሚይዙ የደም ግፊትና የኮሌስትሮል በሽታ እንዳይዘን ይረዳሉ ።

5ኛ፦ ዋልነትስ ጥሩ የማግኒዝየም፣ መዳብና ማንጋኒዝ ምንጭ ሲሆኑ የልብን ጤና ለመጠበቅ ከሚረዱ ምግቦች ይመደባሉ። በተጨማሪም ግፊትንና የኮሌስትሮል በሽታን ይከላከላሉ። እኛ ሀገር በብዛት አላየኋቸውም።

6ኛ፦ ቦለቄ ቦለቄ በውስጡ የማይፈጭ ቃጫ ነገር በመያዙ የሰውነትን የቅባት መጠን በማስተካከል የልብን ጤና ለመጠበቅ ይረዳል።

7ኛ፦ቲማቲም ቲማቲም ላይኮፔን በተባለ የአንቲ ኦክሲዳንት ንጥረ ነገር የታጨቀ በመሆኑ ለልብ ጤና ተመራጭ ምግብ ነው። እንደ ብግነት፣ ካንሰርና ደም ግፊት ላሉ ችግሮችም ይረዳል።

8ኛ፦ያልተቀነባበሩጥራጥሬዎች( whole grains) በፋብሪካ ያልተቀነባበሩ አጃ፣ስንዴ ፣ ገብስ ፣ ሩዝ ከፍተኛ የቃጫ መጠን ስላላቸው አላስፈላጊ ቅባትን በመቀነስ  የደም ግፊትና የልብ ድካም ለመቀነስ ይረዳሉ።

9ኛ፦ነጭ ሽንኩርት ከሚሰጣቸው በርካታ ጥቅሞች ውስ የደም ግፊት መቀነስና የልብ ድካም መከላከል ጥቂቶቹ ናቸዉ ።

10ኛ፦ የምግብ የወይራ ዘይት (olive oil)
ጥሩ ቅባት ስለሚይዝ የደም ግፊትና የልብ ጤናን ለመጠበቅ ይረዳል ።